"ኡቡንቱ" (የጦሳ ቃል) አፍሪካዊያን ህይወትን የሚያዩበትን፣ በተለይም በማህበራዊ ኑሮ ላይ የተመሰረተውን፣ ፍልስፍና ያሳያል። ኡቡንቱ፣ በክብ የሚመሰል፣ ሁሉን ኣካታች መራሄ-ህይወት ነው። የኪናዊ ጉዞዬ ምርኩዝ ላደርገው እሞክራለሁ። "ፑልቶ" በጋሞኛ ቋንቋ ምንጭ ማለት ነው። ወደ ራስ ማንነት፣ ወደ ምንጩ፣ መመለስንና ለጤናማ የህይወት ፍስሰት በማያቋርጥ የመስተጋብርና የለውጥ ሂደት ውስጥ መሆንን ያመለክታል። "ኡቡንቱ 'ና ፑልቶ" የኣፍሪካዊ ማንነት መሰረትን፣ ኡቡንቱን፣ ያልለቀቀ ጤናማ የአስተሳሰብ ዕድገትን፣ የባህል ልውውጥን፣ የለውጥንና የተሃድሶ ሂደትን፣ ለማመልከት የተበጀ እሳቤ ነው። በስራዎቼ፣ “ኦ’ታም ፑልቶ” (በጋሞኛ፣ ኦይዲ-ታም፡ ኣርባ፣ ፑልቶ፡ ምንጭ) በሚል ስያሜ መጠራትን የመረጥኩትም ከዚህ ፍልስፍና ጋር በተያያዘ ምክንያት ነው። ህጋዊ ስሜ ስንቅነህ እሸቱ ነው።
ጀግና መቼም ይወደዳል በሕይወት ሰሳለ ግን ፈተናው ይበዛል ምነው ቢሉ ጅግና ለወዋጭ ነወዋ! አብዮተኛ ነወዋ! ባሕል ልማድ ዕውቀት አኗኗር ሳይበግረው አዲስነትን የሚላበስና የሚያራምድ ጀግና ነዋ! አንድ ጀግና ባሕል ልማድ ሕግና ሥርዓት እንዲሁም በወቅቱ ያለው ዐዕወውቀተት እንዲለወጥም እንዲሻሻልም እንዲያድግም ሲነሳ ማን ዝም ብሎ ያየዋል? ይፈትነዋል ያሳድደዋል ይጨቁነዋል ያሰቃየዋል ተስፋ ያስቆርጠዋል......ብዙ ብዙ በደል፡፡ ጀግና ግን ጀግና ነው ምንም አይበግረው !! ለጀግንነቱ ከገኘው መለኮታዊ ሁለንተናዊነት( በነ ገራችን ላይ እኔ የምገልጸው ጀግና መለኮታዊ ምሳጤና ዕውቀት የነወጠውን ከውስን ዕውቀት የተላቀቀውን ነው) በቋሚነትና በዘላቂነት ኃይልንና ብርታትን እየተማጸነና እየተቀበለ፤ ዘራፈፍ እያለ እቢኝ እያለ እያቅራራ እየፎከረ ለውጥን አዲስነትን የሚያራምድ ሆነ ጀግና፡፡ይህ ታዲያ ለእያንዳዳችን የተሰጠ ፀጋ ነው፡፡ ስለዚህ ሁላችንም እንነሳ ነፍሳችንን እናንቃ እንጠይቃት አንፍራ፤ ከዛም የነፈፍሳችንን ጥያቄ ምላሻ ፍለጋ እንመርምር እንፈልግ ምህላ ግን እንጨምርበት ነፍሳችን ከፍለጋዋ ጋር እንድትገጥምና እንድትረካ፡፡ ያለንበት የምንኖርበት ያወቅነው ዕውቀተት አይገድበን ወይንም ደግሞ አይኮፍሰን፡፡ አንፍራ ጀግና እንሆን ዘንድ አቅምና መለኮታዊ እርደታ አለንና፡፡ ምን ያስፈልግና ነው ወይንም ምን ሆንኩና ነው አንበል ዙሪያችንን አገራችንን ዓለማችንን በጥልቀት አጢን ሁላችን ታመናል ልክፍት ይዞናል፤ ረሃብ ጦርነት ድህት አደንዝዞናል፡፡ በሥጋም በነፍስም አዘቅት ውጦናል፡፡ ታዲያ ዝም እንላለልን ማን ጀግን እንዲሆንልን እንጠብቃለን ጀግናው እራሳችን ሆነን፡፡ ጀግንነታችን በውስጣችን ታፍኖ ታምቆ ሲሰቃይ በጊዜያዊነት ተጨቁኖ በፍርሃት ታስሮ ሲሰቃይ እረ እንነሳ ጎበዝ !!!!
ጀግና መቼም ይወደዳል በሕይወት ሰሳለ ግን ፈተናው ይበዛል ምነው ቢሉ ጅግና ለወዋጭ ነወዋ! አብዮተኛ ነወዋ!
ReplyDeleteባሕል ልማድ ዕውቀት አኗኗር ሳይበግረው አዲስነትን የሚላበስና የሚያራምድ ጀግና ነዋ! አንድ ጀግና ባሕል ልማድ ሕግና ሥርዓት እንዲሁም በወቅቱ ያለው ዐዕወውቀተት እንዲለወጥም እንዲሻሻልም እንዲያድግም ሲነሳ ማን ዝም ብሎ ያየዋል? ይፈትነዋል ያሳድደዋል ይጨቁነዋል ያሰቃየዋል ተስፋ ያስቆርጠዋል......ብዙ ብዙ በደል፡፡
ጀግና ግን ጀግና ነው ምንም አይበግረው !! ለጀግንነቱ ከገኘው መለኮታዊ ሁለንተናዊነት( በነ ገራችን ላይ እኔ የምገልጸው ጀግና መለኮታዊ ምሳጤና ዕውቀት የነወጠውን ከውስን ዕውቀት የተላቀቀውን ነው) በቋሚነትና በዘላቂነት ኃይልንና ብርታትን እየተማጸነና እየተቀበለ፤ ዘራፈፍ እያለ እቢኝ እያለ እያቅራራ እየፎከረ ለውጥን አዲስነትን የሚያራምድ ሆነ ጀግና፡፡
ይህ ታዲያ ለእያንዳዳችን የተሰጠ ፀጋ ነው፡፡ ስለዚህ ሁላችንም እንነሳ ነፍሳችንን እናንቃ እንጠይቃት አንፍራ፤ ከዛም የነፈፍሳችንን ጥያቄ ምላሻ ፍለጋ እንመርምር እንፈልግ ምህላ ግን እንጨምርበት ነፍሳችን ከፍለጋዋ ጋር እንድትገጥምና እንድትረካ፡፡ ያለንበት የምንኖርበት ያወቅነው ዕውቀተት አይገድበን ወይንም ደግሞ አይኮፍሰን፡፡ አንፍራ ጀግና እንሆን ዘንድ አቅምና መለኮታዊ እርደታ አለንና፡፡ ምን ያስፈልግና ነው ወይንም ምን ሆንኩና ነው አንበል ዙሪያችንን አገራችንን ዓለማችንን በጥልቀት አጢን ሁላችን ታመናል ልክፍት ይዞናል፤ ረሃብ ጦርነት ድህት አደንዝዞናል፡፡ በሥጋም በነፍስም አዘቅት ውጦናል፡፡
ታዲያ ዝም እንላለልን ማን ጀግን እንዲሆንልን እንጠብቃለን ጀግናው እራሳችን ሆነን፡፡ ጀግንነታችን በውስጣችን ታፍኖ ታምቆ ሲሰቃይ በጊዜያዊነት ተጨቁኖ በፍርሃት ታስሮ ሲሰቃይ እረ እንነሳ ጎበዝ !!!!