Wednesday, October 28, 2015

AN ANGEL KILLER/መልዓክ ገዳይ!

Do you sometimes feel like you want to cry or weep or feel totally uncomfortable for apparently no reason? Frowning, someone somewhere might have killed an angel. This then is opposite to the contagiousness of joy. A little smile, please.

አንዳንዴ ከሜዳ ተነስቶ ብስጭት ብስጭት፣ ጭንቅ ጭንቅ፣ ይልሻል? ወይም ጩሂ ጩሂ፣ ኣልቅሺ ኣልቅሺ ይልሻል? ወይም እንዲሁ እረፍትና ምቾት ሳይሰማሽ ይውላል? እንግዲያው፣ የሆነ ቦታ የሆነ ሰው ፊቱን ኣጉል ኣጨፍግጎ ያንድ መልዓክ ሞት ምክንያት ሆኖ ይሆናል (አርባ ጠብታዎችሕብረ-ነፍስለምታውቋት፣ ይህ የዚያ ተቃራኒ መሆኑ ነው፡፡) ያለምክንያት የሚሆን ነገር የት ኣለ! ትንሽ ፈገግታ፣ እባክህ!


Sunday, October 25, 2015

What is the Source of Your Mother’s (s’) Powers?

Everyone has a story to tell. Almost everyone has a story to tell about his/her mother. Setaweet offered me the privilege of speaking at their next open session. The topic of the talk is yet to be fixed. My interest, I suggested, is on the roles and powers of women I am trying to explore in my works. “Catch Your Thunder,” for example, is a story about the rise of women leaders the like of Hendeke, Sheba, and Nyabinghi. My perspective on women (or feminism) is as much shaped by my mother and grandmother as is by my religion. I am trying to find a wider cultural foundation for the former influences. My mother was loved and respected by many. She was friends to all irrespective of religion or social standing, even to beggars and street scare-figures. I imagine her influence is equal to the degree of love she won over hearts. And she was not a declared philanthropist or political activist. She was just a mother. Even at home her powers were exercised in her motherly ways. Do I see her qualities in the current women leaders that are considered role models? Rarely. These days, models of women to which many of us have difficulty to associate to are being imported. I wonder if we do not need a different model of women than what the popular media is trying to force on us. That gave me a riddle I am trying to unravel for a long time now: what is a powerful woman made of? How should these powers be exercised for the benefit of all? My stories are replete with tales of women that I think are powerful. You sure have your own models of strength and different stories to tell. It would be great if you could share that with us so that we may see if we could forge an alternative model(s) of a powerful woman. Shall we begin with this: where does the power of your mother come from? Based on that, what qualities would you like to see in our women leaders?

የእናትህ/ሽ ኃይል ምንጩ ምንድነው?

እያንዳንዱ ሰው ሊናገረው የሚሻው ታሪክ ኣለው፡፡ ኣብዛኛው ሰው ስለእናቱ የሚናገረው ታሪክ ኣለው፡፡ ሴታዊት (https://www.facebook.com/Setaweet-336495249877408) በመጪ ፕሮግራማቸው ላይ እናገር ዘንድ ዕድሉን ሰጡኝ፡፡ እምናገርበት ርዕስ ገና ኣልተወሰነም፡፡ በበኩሌ፣ በሥራዎቼ በማሰስ ላይ ስላለሁት የሴቶች ኃይልና ሚና ብናገር ደስ እንደሚለኝ ሃሳብ ኣቀረብኩ፡፡ “ካች ዩር ተንደር/Catch Your Thunder፣” ሕንዴኬን፣ ሳባን፣ እና ኒያቢንጊን ስለመሳሰሉ ኃያል ሴቶች ዳግመ-ትንሳዔ የሚያወራ ተረክ ነው፡፡ ስለሴቶች ያለኝ ዕይታ በኣመዛኙ የተቀረፀው በእናቴ፣ በኣያቴ፣ እና በእምነቴ ነው፡፡ በሥራዎቼ ውስጥ እናቶቼ ላሳደሩብኝ ተፅዕኖዎች ሰፊ ባህላዊ መሠረት ለማግኘት እየሞከርኩ ነው፡፡ እናቴ በብዙ ሰዎች የተወደደች የብዙዎች እናት ነበረች፡፡ ሃይማኖትና የኑሮ ደረጃ ሳይለይ ብዙዎች ወዳጆቿ ነበሩ፤ የጎዳና ላይ የኔብጤዎችን እና ኣስፈራሪዎችን ጨምሮ፡፡ የተፅዕኖዋም ልኬት የተወዳጅነቷን ያህል እንደሁ ኣስባለሁ፡፡ ግን፣ እሷ የታወጀላት ግብረሰናይ ወይም የሆነ ማኅበር መሪ ኣልነበረችም፡፡ በቃ፣ እናት ነበረች፡፡ በቤት ውስጥም ቢሆን ተፅዕኖዋ የሚከወነው በእናታዊ መንገዶቿ ነበር፡፡ የሷ ባህሪያት ዛሬ እንደሞዴል በምንወስዳቸው ሴት መሪዎቻችን ውስጥ ይታያሉ? በትንሹ፡፡ ዛሬ፣ ከሌሎች ባህሎች የሴትነት ሮል ሞዴሎች (የሚና ተምሳሌቶች) ወደኛ ባህል ሲሰርጉ እናያለን፡፡ ብዙዎቻችን እነዚያን ሞዴሎች በቤታችን እና በመንደራችን ውስጥ ከምናውቃቸው ልባም/ኃያል ሴቶች ጋር ለማጣጣም ይከብደናል፡፡ ብዙውን ጊዜ፣ “መገናኛ ብዙሃን ሊጭኑብን ከሚፈልጉት የሴትነት ሞዴል የተለየ ሞዴል ኣያስፈልገን ይሆን እንዴ?” ብዬ ኣስባለሁ፡፡ ያ ከረጅም ግዜ ጀምሮ ልፈታው ጥረት በማድረግ ላይ ያለሁትን እንቆቅልሽ ሰጠኝ፡- ኃያል ሴት፣ ልባም ሴት፣ የተሰራችው ከምንድነው? ኃይሏ መተግበር ያለበትስ እንዴት ነው? የምፅፋቸው ታሪኮች እኔ ጠንካራ በምላቸው ሴቶች የተሞሉ ናቸው፡፡ ኣንተም/እንቺም ኃያል የምትላ/ያት ሌላ ዓይነት ሴት፣ ልትናገረ/ሪው እምትሻ/ሺው ሌላ ታሪክ መኖሩ እርግጥ ነው፡፡ ይህንን ታሪክህ/ሽን ልታጋራ/ሪን ብትችል/ዪ መልካም እንደሚሆን አሰብኩ! ምናልባት ኣማራጭ የሴትነት ሞዴሎችን ማግኘት እንችል ይሆናል፡፡ ምናልባትም የሴታዊት ውይይታችን በዚህ ዳብሮ ሊቀርብ ይችል ይሆናል፡፡ በዚህ ብንጀምርስ፡ የእናትህ/ሽ ኃይል ምንጩ ምንድነው? ወይም፣ ጥንካሬዋ እምን ላይ ነው? ከዚህ በመነሳት፣ በሴት መሪዎቻችን ውስጥ ማየት የምትፈልገ/ጊው ባህሪይ ምንድነው?

Tuesday, October 20, 2015

እምቢም እሽም ማለት ጦርነት ማለት ሲሆን!

ኣንዳንዴ ኣንዳንድ ሰዎች እምቢኝ! ይላሉ። ጥቂት ማጉዳዊያን የማኅበረሰባቸውን ጉልጢምጢሚት እየመዘመዘ ላለው የባህል “ኣልሳይመርስ” (ደዌ-ዝንጋዔ) እምቢኝ! ኣሉ። ጉዳያቸው ያ ብቻ ኣይደለም። እማይታለፍ እሚመስለውን የምፅዓት ፈተና ኣልፈው መታረሷ በማይቀረው በዚህች ኣሮጌ ዓለም ላይ የጥንታዊ ጥበባቸውን ዘር መዝራት ኣለባቸው። ይህ፣ እሺ! ነው። ይህ “እሺ!” እና ያ “እምቢ!” ጊታ ዖላን ማለት ሆነ። ጊታ ዖላ (የጋሞኛ ቃል ነው) - ታላቁ የምፅዓት ጦርነት ነው! የሚጋፈጡኣቸው ኃይላት እጅግ ግዙፍና ጠቅላይ-ዓለም ናቸው። ደንታ ኣላቸው ማጉዳዎች! እነሱ፣ ሙታንን እና ግማሽ-ሙታንን ለማዘዝ የሚያስችላቸውን ጥንታዊውን ጥበባቸውን ገና ኣልረሱም። ወዲያኛው ዓለም፣ ትዕዛዝ የሚጠብቁ ከመቶ ቢሊዬን በላይ ሙታን የሚርመሰመሱበት የጦር ካምፕ መሆኑን ስናስብ፣ ሊመጣ ያለው ጦርነት የትኛውንም ዓይነት የኣርማጌዶን ተረክ ማጠንዛቱ ኣይቀርም። እንግዲህ፣ “Rendezvous with the End” (የምፅዓት ቀጠሮ) የዚህ ታላቅ ጦርነት የጅማሮ ተረክ ነው። እንደፈቃዱ፣ ቢያንስ ኣራት መፅሃፎች ይከተሉታል።

WHEN BOTH "YES" AND "NO" MEAN WAR!

Some people sometimes say NO! A few Magudan’s said no to the cultural Alzheimer’s eating upon the marrows of their society. That is not their only issue. Against all odds that the impending catastrophe may entail, they have to plant the seeds of their ancient wisdom on the old world about to be plowed under. This is YES! This YES and their NO meant the Gita Ola – the Great Apocalyptic Battle. The forces they are about to face are colossal and world-scale. Do they care? They are among the few who didn’t yet forget the ancient art of commanding the dead and the half-dead. Considering that the other world is a military camp swarming with over hundred billion dead people waiting to take orders, the ensuing battle would pale any tale of Armageddon. “Rendezvous with the End” is the tale of the beginning of this epic battle. God willing, at least four more books will follow it.  

Sunday, October 18, 2015

Discover the Ring of Power/ሐሰሳ ሚስጥረ-ኢትዮጵያ

እነሆ በፌስ ቡክ ላይ ለቅምሻ ማጋራት የጀመርሁትን የ“ካች ዩር ተንደር” አንዳንድ ጥቅሶችን በጦማሬም ላይ መለጠፍ ቀጠልሁ፡
Quotes from my latest novel "Catch Your Thunder: Rendezvous with the End" that I am sharing on my facebook page, I started to post on my blog also. Shall we start from here: