"ኡቡንቱ" (የጦሳ ቃል) አፍሪካዊያን ህይወትን የሚያዩበትን፣ በተለይም በማህበራዊ ኑሮ ላይ የተመሰረተውን፣ ፍልስፍና ያሳያል። ኡቡንቱ፣ በክብ የሚመሰል፣ ሁሉን ኣካታች መራሄ-ህይወት ነው። የኪናዊ ጉዞዬ ምርኩዝ ላደርገው እሞክራለሁ። "ፑልቶ" በጋሞኛ ቋንቋ ምንጭ ማለት ነው። ወደ ራስ ማንነት፣ ወደ ምንጩ፣ መመለስንና ለጤናማ የህይወት ፍስሰት በማያቋርጥ የመስተጋብርና የለውጥ ሂደት ውስጥ መሆንን ያመለክታል። "ኡቡንቱ 'ና ፑልቶ" የኣፍሪካዊ ማንነት መሰረትን፣ ኡቡንቱን፣ ያልለቀቀ ጤናማ የአስተሳሰብ ዕድገትን፣ የባህል ልውውጥን፣ የለውጥንና የተሃድሶ ሂደትን፣ ለማመልከት የተበጀ እሳቤ ነው። በስራዎቼ፣ “ኦ’ታም ፑልቶ” (በጋሞኛ፣ ኦይዲ-ታም፡ ኣርባ፣ ፑልቶ፡ ምንጭ) በሚል ስያሜ መጠራትን የመረጥኩትም ከዚህ ፍልስፍና ጋር በተያያዘ ምክንያት ነው። ህጋዊ ስሜ ስንቅነህ እሸቱ ነው።
I wrote the same thing once--- and I gave for those who said these--- they despised me... hahaand they proved me what they meant by 'Nebern'
I wrote the same thing once--- and I gave for those who said these--- they despised me... haha
ReplyDeleteand they proved me what they meant by 'Nebern'