ኣንዳንዴ ኣንዳንድ ሰዎች እምቢኝ!
ይላሉ። ጥቂት ማጉዳዊያን የማኅበረሰባቸውን ጉልጢምጢሚት እየመዘመዘ ላለው የባህል “ኣልሳይመርስ” (ደዌ-ዝንጋዔ) እምቢኝ! ኣሉ።
ጉዳያቸው ያ ብቻ ኣይደለም። እማይታለፍ እሚመስለውን የምፅዓት ፈተና ኣልፈው መታረሷ በማይቀረው በዚህች ኣሮጌ ዓለም ላይ የጥንታዊ
ጥበባቸውን ዘር መዝራት ኣለባቸው። ይህ፣ እሺ! ነው። ይህ “እሺ!” እና ያ “እምቢ!” ጊታ ዖላን ማለት ሆነ። ጊታ ዖላ (የጋሞኛ
ቃል ነው) - ታላቁ የምፅዓት ጦርነት ነው! የሚጋፈጡኣቸው ኃይላት እጅግ ግዙፍና ጠቅላይ-ዓለም ናቸው። ደንታ ኣላቸው ማጉዳዎች!
እነሱ፣ ሙታንን እና ግማሽ-ሙታንን ለማዘዝ የሚያስችላቸውን ጥንታዊውን ጥበባቸውን ገና ኣልረሱም። ወዲያኛው ዓለም፣ ትዕዛዝ የሚጠብቁ
ከመቶ ቢሊዬን በላይ ሙታን የሚርመሰመሱበት የጦር ካምፕ መሆኑን ስናስብ፣ ሊመጣ ያለው ጦርነት የትኛውንም ዓይነት የኣርማጌዶን ተረክ
ማጠንዛቱ ኣይቀርም። እንግዲህ፣ “Rendezvous with the End” (የምፅዓት ቀጠሮ) የዚህ ታላቅ ጦርነት የጅማሮ ተረክ
ነው። እንደፈቃዱ፣ ቢያንስ ኣራት መፅሃፎች ይከተሉታል።
No comments:
Post a Comment